ድርጅቱ የተቋቋመበት ዓላማ

ፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 25/84 መሰረት  የከርሰ ምድር ፍልውሃን በመጠቀም  ለመታጠቢያ አገልግሎት፣ ለመዝናኛ ፣ ለፈውስ አገልግሎት፣ ለመታሻ ፣ ለሳውና ባዝ  እና ለእንፋሎት መታጠቢያ አገልግሎት እንዲሁም ለተዛማጅ የሆቴል አገልግሎት እንዲውል ነው፡፡

የድርጅቱ ራዕይ

በሃገሪቱ በተፈጥሮ ፍልውሃ መታጠቢያ በስፓ በሆቴል አገልግሎት ግንባር ቀደምና ተመራጭ ሆኖ ማየት፡፡

የድርጅቱ ተልዕኮ

ድርጅቱን ዘርፈ ብዙ አገልግሎት ማለትም ደረጃውን የጠበቀ የመታጠቢያ ፣ የፊዚዮቴራፒ ፣ የሳውና ባዝ ፣ የስቲም ባዝ ፣ ህክምና ፣ የሆቴል፣ የመናፈሻ እና የመሰብሰቢያ አዳራሽ አገልግሎቶቻችንን በብቃት  በጥራት በመስጠት የተጠቃሚውን  ህብረተሰብ ፍላጎት ማርካት እና የቱሪዝም መዳረሻ እንዲሆን በማስቻል የሃገሪቱን የእድገትና ትራንስፎርሜሽ ዕቅድ ለማሳካት የበኩሉን ድርሻ መወጣት ነው ፡

እሴት

 ደንበኛ የህልውናችን መሰረት ነው ፣

የደንበኞቻችንን አስተያየት መቀበልና ስህተታችንን በማረም ደንበኞችን ማርካት 

•በተነሳሽነት ፣ በቁርጠኝነትና በጋራ ስሜት ለውጤት መስራት 

•የአገልግሎት ጥራትና የመስተንግዶ  ቅልጥፍና ተቀዳሚ ተግባራችን ነው፣

•በግልፅነትና ታማኝነት ላይ የተመሠረተ ቀልጣፋና የደንበኞችን ጊዜ የሚቆጥብ አገልግሎት መስጠት